ከስድስት አመት ከአምስት ወር ከሁለት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት ቀን  እስር በኃላ ዛሬ በነፃ ተለቀቀ

ከስድስት አመት ከአምስት ወር ፣ ከሁለት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት ቀን  በፊት፣ አገሩንና ሕዝቡን በመዉደዱ፣ የዜጎች ሕመም የኔም ሕመም ነው በማለቱ ሕጻናት ልጆቹን ከትምህርት ቤት ሊቀበል እየጠበቀ ሳለ አዋክበው፣ አፍነው ወሰዱት። በሕወሃት ኢትዮጵያ፣ ለሕዝብ መቆምና መልካም ማድረግ እንደ “ሽብርተኝነት” የሚያስከስስና የሚያሳስር በመሆኑ፣ ገዢዎች የፈለጉት ከማሰር፣ ከመገደል ፣ ከማሸማቀቅ ወደ ኋላ ስለማይሉ፣ እርሱን “ሽብርተኛ ነህ” ብለው፣ ምስክሮች አስጠንተው፣ ለዳኞች ቀጥተኛ መመርያ ሰጠው ፈረዱበት። የእድሜ ልክ እስራት። ተወዳጁ አንዱዋለም አራጌ የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመመበር።

Free at last!!! after six and half years’ imprisonment

አንዱዋለም በወህኒ ቤት ብዙ ጊዜ ድብደባ ተፈጽሞበታል። ጨለማ ቤት አሳድርዉታል። ሞራሉ ለመስበርና ተስፋ ሊያስቆርጡት ብዙ ሞክረዋል። እርሱ ግን በአካል ከፍተኛ ጉዳት ቢደርስበትም፣ ከልጆቹ፣ ከባለቤቱ መለያየቱ ውስጡን ቢያሳምመውም፣ አንገቱን አልደፋም። በአካል ቢያስሩትም በመነፈሱ ነጻ በመሆኑ ከወህኒ ቤት “ያልተኬደበት መንገድ” በሚል ርእስ ሕዝብ ለመበቱና ለነጻነቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዴት መታገል እንዳለበት አቅጣጫ የሚያሳየ መጽሕፍ አስነብቦናል። ከአምስት አመት በፊት ከወህኒ ሆኖ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባስተላለፈው መልእክት እስረኞች እንዲፈቱ ህዝቡ እያደረገ ያለውን ትግል አመስግኖ፣ ነጻነት በትግል እንጅ በአዋጅ እንደማይመጣ ነበር የገለጸው።

“ ነፃነት ማንም በችሮታ ወይንም በአዋጅ የሚያረጋግጥልን ሳይሆን በነፃነት ለነፃነት የተፈጠርን ሉዓላዊ ፍጡራን መሆናችንን ከልብ ስናምን የምንጎናፀፈው ፀጋ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ትልቁ የነፃነት ጠላት እራስን ዝቅ አድርጎ ከማየት የሚመጣፍርሃት ነው፡፡ ፍርሃትን ያላሸነፈ ሕዝብ በአዋጅ ነፃ ሊወጣ አይችልም፡፡ አዋጅ መች ቸገረንና? ፍርሃትን ያላሸነፈ ህዝብ የነፃነቱ ባለቤት ሊሆን አይችልም፡፡ ፍርሃትን ያላሸነፈ ህዝብ ለልጆቹ ነፃ ሀገር ሊያወርስ አይችልም፡” ነበር ያለው አንዱዋለም ከቃሊቲ እስር ቤት።

ቀደም ሲል በመላው አገሪቷ በሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ፣ ላለፉት ሁለት አመታት ደግሞ በኦሮሚያና በአማራው ክልል በተነሱ መጠነ ሰፊ የለውጥ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ፣ ሕዝብ ገዢዎችን ታግሎ በማስገደዱ፣ የፈጠሪም ቸርነት ተጨመሮበት፣ አንዱዋለማራ አራጌ ዛሬ፣ ከነጀግናው እስክንድር ነጋ፣ ናትናኤል መኮንን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ጀግኖቻችን ጋር ከወህኒ ተለቋል።

አንዱዋለም አራጌና ከወህኒ የተፈቱ ጀግኖቻችን እንኳን ለቤታችሁ አበቃችሁ እንላለን። ቤተሰብ ፣ ዘመድ አዝማድ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ። ሁሉም የሕሊና እስረኞች ሁሉ እንዲፈቱ ስንጮህና ስንደክም  ለነበርን ኢትዮጵያዊይን ሁሉ እንኳን ደስ ያለን። ተደብቀው፣ ሸምቀው ነበር አፍነው የወሰዱት። ዛሬ ግን አንዱዋለም በክብር፣ በአገራችን ሰንደቅ አሸብርቆ በብዙ ሕዝብ ታጅቦ ወጥቷል።

ትግሉ እስረኞችን በመፍታት አያበቃም። አገር ከ እስራት እስካልተፈታች ድረስ ትግሉ አያቆምም።ከዚህ በኋላም በአገራችን ማንም ዜጋ በፖለቲካ አመለካከቱ እንደማይስታሰር ዋስታና ያለባት አገር እስክትሆን ድረስ  የበለጠ ትግላችንን ማጠናከር የግድ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

Filed in: News
Find us

You might like:

ለሚገባችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬ ከክብሮትና ፍቅር ጋር ይድረሳችሁ…. (አንዱዓለም አራጌ) ለሚገባችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬ ከክብሮትና ፍቅር ጋር ይድረሳችሁ…. (አንዱዓለም አራጌ)
Ethiopia releases journalist, politician, drops blogger charges Ethiopia releases journalist, politician, drops blogger charges
ከስድስት አመት ከአምስት ወር  ከሁለት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት ቀን  እስር በኃላ ዛሬ በነፃ ተለቀቀ ከስድስት አመት ከአምስት ወር ከሁለት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት ቀን  እስር በኃላ ዛሬ በነፃ ተለቀቀ
ብርቱው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ቆራጡ ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 760 የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ ተብሏል! (በጌታቸው ሺፈራው) ብርቱው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ቆራጡ ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 760 የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ ተብሏል! (በጌታቸው ሺፈራው)

Leave a Reply

Submit Comment

© 2018 Free Andualem Aragie. All rights reserved. / Valid.
Proudly designed by www.freeandualemaragie.org.