በግፍ የተገፋው የአማሮቹ ልጅ!! እንደ ኢትዮጲያዊነቱ ታግሎ ሳለ በአማራነቱ መከራው የበዛበት አንዱአለም አራጌ! !!!

መንግስቱ ዘገየ

አንተ የተገፋሃው የአማሮቹ ልጅ! !! ጅምር ፍቅርህን ሳታጣጥም ፤ ባባ የሚሉ እንቡጥ ልጆችህን ስመህ ሳትጠግብ ለነደኔ አይነቱ ግብዝና ራስ ወዳድ ኢትዮጲያዊ ብለህ ሺ እጥፍ ድርብ ዋጋ የከፈልከው የአርሶ በሌው የጋይንቴው መብረቅ! !!! ወደ ወህኒ ከወረወሩህ ጊዜ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ስላንተ ልጽፍ አስብና እምባ እየቀደመኝ እቸገራለሁ ። ከራማህ ሁልጊዜ እየመጣ ስለምንድን እኔ የአማራይቱን ልጅ ረሳሃኝ እያለ ያንገላታኛል ። በእውነት ሰሞኑን መንፈሴ ስለ አንዱአለም አራጌ የማትመሰክር አንተን ብሎ አማራ እያለ ይሞግተኛል ። ግን ዛሬ የኢትዮጲያ አምላክ ምስክር ይሁንብኝ ይችን ሶስት መስመር ስጽፋ እንኳን በሁለቱም አይኖቼ እምባየ ዘለላ ሆኖ እየፈሰሰ ነው ። አንዱአለም ብረሳህ የአማሮቹ አምላክ ይርሳኝ! !!!!

አንተና መሰሎችህ በከፈላችሁት መስዋእትነት የነጻነት ጸሃይ ዳግም ላትጠልቅ ወጥታለች! !!! ቀይ ባህርን ካሻገርከን በሃላ የግብጽ ሽንኩርት የሚናፍቀን ነፍረቆች ሳንሆን የከነአንን ቅጥርና ረጃጅም ዘቦቿን ጥሰን ከተማዋን የምንወርስ ጃውሳዎች የኢያሪኮን ግንብ ደርምሰን ርስታችንን ለማስመለስ እስከወዲያኛው ድረስ የምንዋደቅ ፋኖዎች ሆነናልና መስዋእትነትህ ከንቱ አልቀረም ።
አንተ ጎበዝ ስምህ በጭቁኖች ልብ በወርቅ ቀለም ተጽፏልና ደስ ይበልህ! !!!

(( በዚህ አጋጣሚ ትንታጉን አንዱአለም አራጌ ያልተሄደበት መንገድ በሚል ርእስ የጻፈውን መጽሃፍ ፈልጋችሁ አንብቡት! !! ወዳጅና ጠላታችንን በቅጡ ለማወቅ ጉጉት ይደርብን እስኪ!)

Filed in: News
Find us

You might like:

ለሚገባችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬ ከክብሮትና ፍቅር ጋር ይድረሳችሁ…. (አንዱዓለም አራጌ) ለሚገባችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬ ከክብሮትና ፍቅር ጋር ይድረሳችሁ…. (አንዱዓለም አራጌ)
Ethiopia releases journalist, politician, drops blogger charges Ethiopia releases journalist, politician, drops blogger charges
ከስድስት አመት ከአምስት ወር  ከሁለት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት ቀን  እስር በኃላ ዛሬ በነፃ ተለቀቀ ከስድስት አመት ከአምስት ወር ከሁለት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት ቀን  እስር በኃላ ዛሬ በነፃ ተለቀቀ
ብርቱው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ቆራጡ ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 760 የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ ተብሏል! (በጌታቸው ሺፈራው) ብርቱው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ቆራጡ ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 760 የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ ተብሏል! (በጌታቸው ሺፈራው)

Leave a Reply

Submit Comment

© 2018 Free Andualem Aragie. All rights reserved. / Valid.
Proudly designed by www.freeandualemaragie.org.