ትውስታ” ልክ የዛሬ 7.አመት አካባቢ ቀበና የሚገኘው የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ግቢ – ስንታየሁ ቸኮል

ትውስታ” ልክ የዛሬ 7.አመት አካባቢ ቀበና የሚገኘው የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ግቢ በርካታ ወጣት በወቅታዊ ውይይት ተጥለቅልቆ ሰፊ የትግል መነቃቃት ይታይ ነበር፡፡

ድንገት ሳይታሰብ አንዳች ነገር ተሰማ …ምድርና ሰማይ የተጣበቀ ይምስላል አመራሩ ተዋከበ …አባሎች በግቢ ውስጥ ስልክ ይደውላሉ ሁኔታው ምን እንደሆነ ከሰዎች ስረዳ ልቤ በሐዘን ተሰበረ፡፡ አንዱአለም አራጌ በስርዓቱ ጋንጩሬ ተወሰደ፡፡ የሚል ዜና ከባድ አደረገው <<ተቃዋሚዎች እግር እስኪያወጡ እንጠብቃለን እግር ሲያወጡ እንቆርጣለን>> በህሊናዬ ተመላለሰ እወነት ነው. አንዱአለም ወደ ሕ/ግ ከመጣ ወዲህ ይህ ነው የማይባል ለውጥ ፍፁም የውስጥ መረጋጋት የእርስ በእርስ ትስስር አምጥቶ ነበር፡፡ አንድነት ፓርቲ በፅኑ መሠረት እንዲቆም ያደረገው እግሩ አንዱአለም ነበር፡፡

የጀርባ አጥንቱ እንደተሰበረ ነገር ከዛ ጊዜ ጀምሮ ፓርቲው ጎብጦ ውስጡ በስልጣን ጥመኞች ተቦርቡሮ በሴረኞች ተንኮል ወደ መቃብር ተሸኘ ፡፡ አንዱአለም የታሰረለት ድርጅት ከማፍረስ ጀምሮ የእድሜ ልክ እስር ተጨማሪ በቀል ፈረዱበት፡፡ መታወቅ ያለበት ግን ጓዳችን ማንም የማይከለክለው ሁሌም በልባችን ይኖራል፡፡

Filed in: News
Find us

You might like:

ዛሬ የጀግናው አንዷለም አራጌ የትውልድ ቀን ነው  7 አመት እስር ቤት ልደቱን አከበረ ዛሬ የጀግናው አንዷለም አራጌ የትውልድ ቀን ነው 7 አመት እስር ቤት ልደቱን አከበረ
UN Declares Detention of Opposition Politician Andualem Aragie Arbitrary; Calls for Release UN Declares Detention of Opposition Politician Andualem Aragie Arbitrary; Calls for Release
በግፍ የተገፋው የአማሮቹ ልጅ!! እንደ ኢትዮጲያዊነቱ ታግሎ ሳለ በአማራነቱ መከራው የበዛበት አንዱአለም አራጌ! !!! በግፍ የተገፋው የአማሮቹ ልጅ!! እንደ ኢትዮጲያዊነቱ ታግሎ ሳለ በአማራነቱ መከራው የበዛበት አንዱአለም አራጌ! !!!
ትውስታ” ልክ የዛሬ 7.አመት አካባቢ ቀበና የሚገኘው የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ግቢ – ስንታየሁ ቸኮል ትውስታ” ልክ የዛሬ 7.አመት አካባቢ ቀበና የሚገኘው የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ግቢ – ስንታየሁ ቸኮል

Leave a Reply

Submit Comment

© 4835 Free Andualem Aragie. All rights reserved. / Valid.
Proudly designed by www.freeandualemaragie.org.