አንዱዓለምና እስክንድር ሰው ናፍቀዋል የሰው ያለህ እያሉ ነው!!!! ዛሬ

1780811_751873094830908_1867964153_n

አቶ ግርማ ሰይፉ የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት

አንዱዓለም አራጌን ለማየት ቃሊቲ ጎራ ብዬ ነበር ፡፡ ቃሊት ሁለት ሰው ማየት ስለማይቻል ከአንዱዓም ጋር የተሳረውን እስክንድርን ማግኘት አልቻልኩም፡፡ አንዱዓለም እና እስክንድርን መጠየቅ የሚቻልበት ሰዓት እጅግ አጭር ከመሆኑ የተነሳ ጠያቂዎቻቸው ተሰፋ እየቆረጡ እነርሱም ሰው እየናፈቃቸው እንደሆነ ሲነግረኝ ልቤ ስብር ብላለች፡፡ ገና ከአሁኑ ጠያቂዎች ወደኋላ ማለት ከጀምርን እነዚህ ልጆች እየከፈሉ ያለውን መሰዋዕትነት ችላ ማለት ብቻ ሳይሆን ሸክሙን ሁሉ ለቤተሰቦች ጥለን ትግል ላይ ነው ያለነው ማለት አይቻልም፡፡

የህሊና እስረኞች ጉዳይ ያገባናል የሚል ሁሉ ጀግኖቻችንን መጎብኝትና ማበረታት የግድ ይላል፡፡ በቅርብ ያሉት በዚህን ያህል የሰው ናፍቆት ካደረባች እሩቅ የሚገኙት እነ ናትናኤልና ሰይፈ ሚካኤል በምን ደረጃ እንደሚገኙ መገመት አያሰቸግርም፡፡ ከወሬ ወጥተን አለን ብንል ምን ይመስላችኋል ጎበዝ …. ዘወትር ከአምስት እሰከ ስድስት ሰዓት የመጠየቂያ ሰዓት መሆኑን ማስተወስ ተገቢ መሰለኝ፡፡

በዚሁ አጋጣሚ እነ ሀጎስ ያለምንም ማጉላላት ከአንዱዓለም ጋር ተገናኝቼ ለ45 ደቂቃ እንድናወጋ በማድረጋቸው ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ እስረኛ መጠየቅ ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን ዘንግቼው ሳይሆን ስታንገላቱኝ መውቀስ ብቻ እንዳይሆን ብዬ ነው፡፡

Filed in: Articles about Andualem
Find us

You might like:

በግፍ የተገፋው የአማሮቹ ልጅ!! እንደ ኢትዮጲያዊነቱ ታግሎ ሳለ በአማራነቱ መከራው የበዛበት አንዱአለም አራጌ! !!! በግፍ የተገፋው የአማሮቹ ልጅ!! እንደ ኢትዮጲያዊነቱ ታግሎ ሳለ በአማራነቱ መከራው የበዛበት አንዱአለም አራጌ! !!!
ትውስታ” ልክ የዛሬ 7.አመት አካባቢ ቀበና የሚገኘው የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ግቢ – ስንታየሁ ቸኮል ትውስታ” ልክ የዛሬ 7.አመት አካባቢ ቀበና የሚገኘው የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ግቢ – ስንታየሁ ቸኮል
መስከረም 03/2004 ዓ.ምን ሳስታውሳት… (አንዷለም -ወ- እስክንድር) – ኤልያስ ገብሩ መስከረም 03/2004 ዓ.ምን ሳስታውሳት… (አንዷለም -ወ- እስክንድር) – ኤልያስ ገብሩ
በኢትዮጵያ እውነትና ፍትህ ከትቢያ የተሻለ ቦታ ቢኖራቸው ኖሮ….                                                                               አንዷለም አራጌ በኢትዮጵያ እውነትና ፍትህ ከትቢያ የተሻለ ቦታ ቢኖራቸው ኖሮ….                                                                               አንዷለም አራጌ

Leave a Reply

Submit Comment

© 2017 Free Andualem Aragie. All rights reserved. / Valid.
Proudly designed by www.freeandualemaragie.org.